አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የውጤት አያያዝ እና የማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሁለት ዙር መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን÷ የውጤት አያያዝ እና የማለፊያ ነጥብም እንደየዙሩ የተለያየ ነው።
በዚህ መሠረትም በመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች የሲቪክስ ትምህርት ፈተና ውጤት ያልተያዘ ሲሆን÷ ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ መሆኑን ተመላክቷል፡፡
ለመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 600፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 500፣ ለአይነ ስውራን ተፈታኞች ከ 400 ተይዟል፡፡
ለሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ደግሞ ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 700፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 600፣ ለአይነ ስውራን ተፈታኞች ከ 500 ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት መያዙ ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ በሁለት ዙር በተሰጠው ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ የውጤት አያያዝ እና የማለፍያ ነጥብንከዚህ በታች ከተያያዘው ምስል ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

