አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል የ2014 ዓ.ም የበልግ ወቅት የግብርና ልማት የንቅናቄ መድረክ በቡታጅራ ከተማ ተካሄደ፡፡
መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ÷ የህዝብ ተቆርቋሪነትና አገልጋይነት የህብረተሰቡን ህይወት በመቀየርና ካለበት የድህነት ደረጃ ለማውጣት በሚደረግ ቁርጠኛ ጥረት የሚገለጽ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ሁሉም አመራርና ባለሙያ ህዝቡ ከድህነት ወጥቶ በራሱ ጥረት ተስፋው እንዲለመልም የማድረግ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት ጠቁመው÷ ለዚህም ህብረታችንን ማጠንከር፣ሰላማችንን ማስጠበቅ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ክልሉ ከፍተኛ የግብርና አቅም ያለው በመሆኑ በአዲስ ዕይታና እሳቤ የትኛውም የልማት ጊዜ ሳይባክን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል።
ኢትዮጵያን ከድህነት ለማውጣት ቁልፉ መሳሪያ ውጤታማ የግብርና ዘርፍ እንደሆነ ገልጸው÷ አማራጮችን የማስፋትና ውጤታማነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ትኩረት የሚሻ ነው ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

