Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በምዕራብ ጎዴይ ተፋሰስ ከ1 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ እንስሳት መኖና የምግብ ሰብል መልማቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ምዕራብ ጎዴይ ፕሮጀክት በ1 ሺህ 804 ሄክታር መሬት ላይ የእንስሳት መኖና የምግብ ሰብል ማልማት መቻሉን የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አህመድ አብዲ ገለጹ፡፡

በክልሉ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ለመቋቋም በሸበሌ ዞን ቤርዓኖ ወረዳ በምዕራብ ጎዴይ ተፋሰስ ፕሮጀክት ላይ የለሙ የእንስሳት መኖ እና የምግብ ሰብልን ለመሰብሰብ ጊዜው መድረሱን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

የመስኖ ፕሮጀክቱ በአርሶ አደር ኅብረት ሥራ ማህበራት፣ በክልሉ እንስሳት ሀብት ቢሮ፣ በግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በኤሌሌ ወረዳና በጎዴይ መስኖ ፕሮጄክት ድጋፍ የተሰራ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version