Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ግብርና ላይ ያተኮረ በ12 ሚሊየን ዩሮ የሚተገበር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኔዘርላንድስ መንግስት በ12 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበርና ግብርና ላይ ያተኮረ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።
 
የኔዘርላንድስ ዋግኒንገን ዩኒቨርሲቲና የግብርና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩትና ከሌሎች አጋር አካለላት ጋር በመተባበር “ስቲችቲንግ ዋገንገን ሪሰርች” በኢትዮጵያ የሚል በግብርና ትራንስፎርሜሽን ላይ ትኩረት ያደረገ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
 
ፕሮጀክቱ አራት ፕሮግራሞችን ያቀፈ ሲሆን÷ 12 ሚሊየን ዩሮ ተመድቦለታልም ነው የተባለው፡፡
በግብርና ዘርፍ ግብዓት ለመሰብሰብ፣ የኢትዮጵያን የምግብ ዋስትና ሊያረጋግጥ የሚችል አዳዲስ አሰራሮችን ለመዘርጋት፣ እውቀትን ለማፍለቅና የተቋማትን አቅም ለመገንባት እንደሚያስችል የዋግኒንገን ዩኒቨርሲቲና ምርምር በኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ዳዊት አለሙ ገልጸዋል፡፡
 
የዋግኒንገን ዩኒቨርሲቲና የግብርና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩትና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በግብርና ምርምርና ልማት ላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ማከናወናቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
 
የምርጥ ዘር ሥርዓት ማሻሻያ፣ የኤክስቴንሽን ሥርዓት ማሻሻያ፣ የሰሊጥ ምርትና ገበያ ማሻሻያ፣ የግብርና ግብይት እንዲሁም የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ፕሮግራሞች በ”ቤኔፊት” አጋርነት ፕሮግራም አማካኝነት ሲያካሄድ ቆይቷል ተብሏል።
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version