አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ የሚስተዋለውን የነዳጅ ዘይት ስርጭት ችግር መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
በውይይታቸውም በክልሉ የሚስተዋለውን የነዳጅ እጥረት እና ስርጭት ችግር ዘላቂ እልባት መስጠት በሚቻልባቸው መገዶች እና መወሰድ በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ መክረዋል፡፡
በዚህ መሰረት በክልሉ በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጣውን ነዳጅ ዘይት ለመከላከል የጸጥታ አካላት የተቀናጀ እና የተጠናከረ ቁጥጥር እዲያደርጉ አቅጣጫ መቀመጡን ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የነዳጅ ማደያ ባለንብረቶች ላይ ተጠያቂነትን ማስፈንና ቁጥጥር እንዲያደርጉ የተመደቡ አካላት ላይም ጠንካራ ክትትልና ተጠያቂነት እንዲኖር ተወስኗል።
ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የምታስገባው የነዳጅ ዘይት በሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከሀገር እንደሚወጣ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

