Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢትዮጵያ እና በኤግሞንት ኢንስቲቲዩት ተቋማት መካከል ትስስር ለመፍጠር  ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በኤግሞንት ኢንስቲቲዩት በሚገኙ ተቋማት መካከል ትስስር ለመፍጠር ውይይት ተካሄደ፡፡

 

በቤልጂየም የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከኤግሞንት ሮያል የዓለም አቀፍ ግንኙነት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሁግ ቻንትሪ ጋር ተወያይተዋል፡፡

 

በውይይታቸውም አምባሳደሯ በኤግሞንት ኢንስቲቲዩት እና በኢትዮጵያ አቻ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

 

ሁለቱ ወገኖች በኤግሞንት ኢንስቲቲዩት እና በኢትዮጵያ በሚገኙ መሰል ተቋማት መካከል ትስስርን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

በቀጣይም በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

 

ወቅታዊ ሁኔታዎችን በሚመለከት በተለይም የኢትዮጵያ መንግስት ሀገራዊ ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር  እየወሰደ ያለውን አዎንታዊ እርምጃ አስመልክቶ ለአምባሳደር ቻንትሪ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

 

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version