Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መገናኛ ብዙኃን እውነተኛ መረጃ የሚያደርሱና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያስጠብቁ ሊሆኑ ይገባል- መሐመድ እድሪስ

አዲስ አበባ፣ መጋት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕብረተሰቡን የመረጃ ፍላጎት ለማድረስ የመገናኛ ብዙኃን መስፋፋት ወሳኝ ቢሆንም ይህ ብቻ ግን በቂ አይደለም ሲሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ ገለጹ።
መገናኛ ብዙኃኑ ከመስፋፋት ባለፈ እውነተኛ መረጃ የሚያደርሱና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያስጠብቁ ሊሆኑ እንደሚገባም ነው አጽንጾት የሰጡት፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት ”እውነተኛ መረጃ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ዓመታዊ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ኮንፈረንስ እየተካሄደ ባለበት ነው።
በጉባኤው አቶ መሐመድ እድሪስ ባደረጉት ንግግር፥ መገናኛ ብዙኃን እውነተኛ መረጃ ለህብረተሰቡ በማድረስ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ማስጠበቅ አለባቸው፤ ይህ አመታዊ ጉባኤ ቀጣይ ለሚገጥሙ ችግሮች ከወዲሁ ለመዘጋጀት እና ካለፉት ትምህርት ለመውሰድ የሚረዱ ገንቢ ሀሳቦች ይነሱበታል ብለዋል፡፡
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ህግ ማስከበር ዘመቻ የውጭ መገናኛ ብዙኃን የዘገባ ትርክታቸው ምን እንደሚመስል እንዲሁም የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ወቅታዊ ሁነቶች ላይ የነበራቸው ሚናን በተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ይደረግበታል።
በሸራተን አዲስ እየተካሄደ ባለው ኮንፈረንስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የመከላከያ ሚኒስት ዶክተር አብረሃም በላይ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ እና ለሌሎች የኢንዱስትሪው ተወካዮች ተገኝተዋል።
በታሪኩ ለገሰ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version