Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሶማሌ ክልል ለህጻናት አገልግሎት የሚውል የህክምና ቁሳቁስ አሰራጨ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ላጋጠመቸው ህፃናት የሚሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ለ180 የጤና ማዕከላት ማሰራጨቱን አስውቋል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ያሰራጨው የህክምና ቁሳቁስ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተዳረጉ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት የሚያገለግል ነው ተብሏል፡፡
የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር መሀሙድ መሀመድ እንደገለጹት÷በክልሉ ከድርቁ ጋር ተያይዞ ለስርአተ ምግብ መዛባት የተዳረጉ ህፃናት የአመጋገብ ስርአት ለማሳደግ ከፍተኛ ስራዎች እየተከወነ ነው ማለታቸውን የክልሉ ነብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version