Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ሁለት ሹመቶችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የደቡብ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የቀረቡለትን ሁለት ሹመቶች በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
 
በዚሁ መሰረት፡-
 
1. አቶ ክፍሌ ዋና – የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ
 
2. አቶ አበራ ኪፔ- የክልሉ ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እንዲያገለግሉ ተሹመዋል፡፡
 
ተሿሚዎቹ ከወረዳ ጀምሮ በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ላይ የሰሩና ልምድ ያካበቱ መሆናቸው ተገልጿል።
 
ሁለቱ የስራ ኃላፊዎች በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ መፈጸማቸው ተመላክቷል፡፡
 
በተጨማሪ ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን እና አባላት ሹመት አፅድቋል።
 
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ ወይዘሮ ወላይቴ ቢተው የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ደርጅት ቦርድ አባል አድርጎ ሹሟል።
 
በቢቂላ ቱፋ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version