Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሰላም የሁሉም ልማት ስራዎች ዋናው መሰረት በመሆኑ በአንድ አቋም ልንሰራበት ይገባል – አቶ እርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላም የሁሉም የልማት ስራዎች ዋናው መሰረት በመሆኑ በአንድ አቋም ልንሰራበትይገባል ሲሉ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እርስቱ ይርዳ ተናገሩ፡፡
 
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡት ወቅት ነው።
 
የክልሉ መንግስትና ህዝብ በክልል ውስጥ ከሚኖሩም ሆነ ከአጎራባች ክልል ህዝቦች ጋር ከዚህ ቀደም እንደነበረው በፍቅር፣ በአንድነትና በሰላም እንዲኖር መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
 
አብሮነትን ማጠናከርና ችግሮችን በውይይት መፍታት ለሰላም መስፈን ዋና መንገዶች ናቸው ያሉት አቶ እእርስቱ፥ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ እና የደቡብ ክልል አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎችን እንቅስቃሴ ለማስቆም ከክልሉ መንግስት ጋር በቅንጅት ይሰራልም ነው ያሉት።
 
የጉጂ እና ኮሬ ህዝብ፣ የጉጂና ጌዴኦ ህዝብ፣ የጉጁና ቡርጂ ህዝብ ለዘመናት አብሮ በፍቅር የኖረ ህዝብ ነዉ፤ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሚፈፅሙትን ትንኮሳዎች ለማስቆም እንደሚሰራም አፅዕኖት ተሰጥተው ተናግረዋል።
 
የአካባቢው ህዝብም ሰላምን ለማስፈ የሚሰሩ ስራዎችን በመደገፍ የበኩሉን ገንቢ ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል።
 
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት ላይ ከምምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ነሰጡበት ወቅት ነው።
 
የክልሉ ህዝብ በአጎራባች ክልሎች ህዝቦች ጋር ከዚህ ቀደም በነበረው ፍቅሩ በአንድነት ሰላም ለማረጋገጥ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
 
አብሮነትን ማጠናከርና ችግሮችን በዉይይት መፍታት የሰላም መስፈን ዋና መንገዶች ናቸዉም ብለዋል አቶ እርስቱ።
 
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝና የደቡብ ክልል አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎችን እንቅስቃሴ ለማስቆም ከክልሉ መንግስት ጋር በቅንጅት ይሰራልም ነዉ ያሉት።
 
የጉጂ እና ኮሬ ህዝብ፣ የጉጂና ጌዴኦ ህዝብ፣ የጉጁና ቡርጂ ህዝብ ለዘመናት አብሮ በፍቅር የኖረ ህዝብ ነዉ፤ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሚፈፅሙትን ትንኮሳዎች ለማስቆም እንደሚሰራም አፅኖት ተሰጥተው ተናግረዋል።
 
የአካባቢው ህዝብም ሰላም ለማስፈን የሚሰሩ ስራዎችን በመደገፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል።
 
በግብርናው ዘርፍ የግብርና ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ንረት በክልሉ ፈተና መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸው፥ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በክልሉ የሚገኝ አንድም መሬት ፆም አንዳያደር ለማድረግበትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
 
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግም በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ እንደሚከናወን የገለጹት አቶ ርዕቱ ይርዳ፥ ምርታማነትን ክፍ በማድረግ በምግብ ዋስትና እራሳችንን ለመቻል ለግብርናው ዘርፍ ሰፊ ጊዜያችንን እንሰጣለን ነው ያሉት።
 
በክልሉ ከ1 ሚሊዮን በላይ አርብቶ አደሮች እዳሉ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ ከስም ያለፈ ኑሯቸው እንዲሻሻል ለማድረግ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
 
በድርቅ አደጋ ጊዜ ክብቶች እንዳያልቁ የመኖ ልማትና የመስኖ ልማት ላይ የተጀመሩ ስራዎች ይከናወናሉ ነው ያሉት።
 
የክልሉን የመሰረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት የበጀት እጥረት ችገር መሆኑን ጠቁመው፥
አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ለመሰረተ ልማቶች ማስፈጸሚያ የ30 ቢሊዮን ብር ፍላጎት መኖሩን ገልፀዋል።
 
የኑሮ ውድነትን ችግር ለመቅረፍ የሚደረገውን ቁጥጥር በማጥበቅ ጠንካራ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብለዋል።
 
ህገ ወጥነትን የሚያስፋፉ ነጋዴዎች ላይ እየተወሰደያለው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የገለፁት።
 
የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍም ክልሉ ባለው ሀብት ላይ የበለጠ እንዲሰማሩ ይደረጋል ብለዋል።
 
የኢንቨስትመንት እድሎችን በመጠቀም ዜጎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ እናመቻቻለን ብለዋል።
 
በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ግንባታቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎችን ችግሮቻቸውን ለይተን ተከታትለን እናስፈፅማለን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ።
 
የክልሉ መስተዳድር በሌብነትና ብልሹ አሰራሮች ላይ ጠንከራ እርምጃዎች እንደሚወስድም አስጠንቅቀዋል።
 
ሌብነትን ለመዋጋት ከህዝባችን ጋር በመሆን በፅኑ አቋም እንታገላለን ሲሉ የገለጹት አቶ እርስቱ፥ የክልሉ አደረጃጀት በሕገ መንግስታዊ መንገድ መልስ እንደሚያገኝም ጠቁመዋል።
 
በቢቂላ ቱፋ
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version