Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት የጉባኤ ውሳኔዎችን በተመለከ ከህዝቡ ጋር ሊወያይ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የጉባኤ ውሳኔዎችን በተመለከ ከህዝቡ ጋር ሊመክር ነው፡፡
 
ብልጽግና ፓርቲ በቅርቡ የመጀመሪያ ጉባኤ ውን ማካሄዱ ይታወቃል፡፡
 
ይህን ተከትሎም በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ጉባኤው ያስቀመጣቸውን ውሳኔዎች በተመለከተ በቀጣይ ጊዜያት ከህዝቡ ጋር ሊወያይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
የውይይት መድረኮችን በጉባኤው የተመረጡ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና በየደረጃው ያሉ አመራሮች የሚመሩ መሆኑን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የሚካሄደው ውይይት በስኬት ይከናወን ዘንድም አስፈላጊው አቅጣጫ መሰጠቱ ነው የተገለጸው፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version