Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ አየር ሃይል የሀገሪቱ አየር ክልል አስተማማኝ ዘብ ነው – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ የአገር ሉአላዊነት አለኝታና የኢትዮጵያ አየር ክልል አስተማማኝ ዘብ መሆኑን የአየር ሃይሉ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለፁ።
 
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ እንዳሉት፥ አየር ሃይል አሁን ላይ በአቪዬሽንና በአየር መከላከያ ዘመኑ የተደረሰበትን ቴክኖሎጂ የሚጠቀምና በብቁ ባለሙያዎችም የተደራጀ ነው።
 
የኢትዮጵያን የአየር ክልል በመጠበቅ ሂደት ዘመናዊና አስተማማኝ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለግዳጅ አፈፃፀም ውጤታማነትም ከቴክኖሎጂው ጋር አብሮ የሚራመድ የሰው ሃይል መገንባቱን ተናግረዋል።
 
የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ የአገር ሉአላዊነት አለኝታና የኢትዮጵያ አየር ክልል አስተማማኝ ዘብ መሆኑን ገልጸዋል።
 
በመሆኑም የኢትዮጵያ አየር ሃይል ከየትኛውም ጊዜ በላቀ መልኩ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎችና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ተቋም ሆኗል ነው ያሉት።
 
የኢትዮጵያ አየር ሃይል የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎችና በወጣቶች እየተገነባ ያለ ጠንካራ ተቋም መሆኑንም ሌትናል ጄነራል ይልማ አስረድተዋል።
 
የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአገሪቱን የአየር ክልል ከመቆጣጠር ባሻገር ተልዕኮዎችን በከፍተኛ በፍጥነትና በውጤታማነት የሚያሳካ የአገር ኩራትና አለኝታ ሆኗል።
 
የኢትዮጵያ አየር ሃይል በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በቀድሞው አጠራር ከታ ሜዳ አሁን ላይ ሀረር ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ1936 ዓ.ም እንደተመሰረተ አዜአ ዘግቧል።
Exit mobile version