Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ ከ679 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ 679 ሚሊዮን 87 ሺህ 375 ብር ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ፡፡
 
ተጨማሪ በጀቱ በክልሉ የተፈጠረውን የፋይናንስ እጥረት ችግር በመቅረፍ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ለማሳለጥ ላቅ ያለ ድረሻ አለዉ ተብሏል።
 
በተለይ በዞኖችና ወረዳዎች ያለዉን የፋይናንስ እጥረት በመቅረፍ የህዘብ አገለግሎት በጥራት እንዲከናወን ያስችላል ነው የተባለው።
 
ምክር ቤቱ በበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ የቀረበውን የተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ 104/2014 መርምሮ አፅድቋል።
 
ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ የክልሉን ትምህርት ኮሌጆች ለማስተዳደር የወጣውን ረቂቅ አዋጅ 193/2014 መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
 
አዋጁ ኮሌጆች ብቁ መምህራንን አሰልጥነው ለማዉጣት እንደሚያስችላቸው ነው በምክር ቤት አባላቱ የተገለፀው።
 
በዚህም በትምህርት ጥራት ላይ የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታትና ብቁ ዜጎችን ለማፍራት እንደሚያስችል ነው የምክር ቤት አባላቱ የተናገሩት።
 
በምክር ቤቱ በማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የቀረበውን የትምህርት ኮሌጆች ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
የክልሉ ምክር ቤት ሲያካሄድ የቆየዉን 6ኛ ዙር 1ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን የክልሉን ተጨማሪ በጀት 679 ሚሊዮን 87 ሺህ 375 ብር በማፅደቅ ነው የተጠናቀቀው።
በቢቂላ ቱፋ
Exit mobile version