የሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የጉባኤ ውሳኔዎችን አስመልክቶ በቅርቡ ከህብረተሰቡ ጋር እወያያለሁ አለ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የጉባኤ ውሳኔዎችን በተመለከተ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር ከፊታችን ዕረቡ ጀምሮ ውይይት ያካሂዳል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ በቅርቡ ያካሄደውን የመጀመሪያውን ጉባኤ ተከትሎ የሶማሌ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ጉባኤው ያስቀመጣቸውን ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በተመለከተ ከህዝቡ ጋር ሊወያይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከህዝብ ጋር የሚካሄዱ የውይይት መድረኮችን በጉባኤው የተመረጡ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና በየደረጃው ያሉ አመራሮች የሚመሩት መሆኑም ታውቋል፡፡
የሚካሄደውን ውይይት አስመልክቶ አስፈላጊው ገለጻ መሰጠቱንም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌ መግለጻቸውን ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

