Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብልግፅና ፓርቲ በመከረባቸው ውሳኔዎቸና አቋሞች ላይ የሚመክር የህዝብ በሐረሪ ውይይት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልግፅና ፓርቲ ባካሄደው የመጀመሪያ ጉባኤ በመከረባቸው ውሳኔዎቸና አቋሞች ላይ የሚመክር የህዝብ የውይይት መድረክ ከመጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ገለጸ።
የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ በሰጡት መግለጫ ÷ “የህዝብ ውይይት መድረኩ ጉባኤው የመከረባቸው መሠረታዊ ጉዳዮችን ህዝቡ እንዲገነዘባቸውና እንዲያዳብራቸው ያስችላል” ብለዋል።
በብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ በተላለፉ ውሳኔዎች ተፈፃሚነት የክልሉ ህዝብ የበኩሉን ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት የውይይት መድረኩ ያግዛልም ነው ያሉት።
በሚካሄዱ የውይይት መድረኮች ከህዝቡ የሚነሱ ሃሳቦችን በመውሰድ በቀጣይ ፓርቲው የሚሰራቸውን ሥራዎች አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንዳለው ነው ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላከተው፡፡
የውይይት መድረኮችን በጉባኤው የተመረጡ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና በየደረጃው ያሉ አመራሮች የሚመሩት ሲሆን÷የክልሉ ህዝብ ውይይቱ የተሳካ እንዲሆን ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version