አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለዩክሬን ተጨማሪ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር የሰብአዊ ድጋፍ ልታደርግ መሆኑን የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን በዛሬው እለት እንዳስታወቁት ቻይና ለዩክሬን ሰብአዊ እርዳታ የሚውል የ 10 ሚሊየን ዩዋን ወይም 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ልታደርግ ነው።
ይፋ የተደረገው የእርዳታ ገንዘብ የዩክሬንን የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት እና የጦርነቱን መባባስ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ቃል አቀባዩ ገልፀዋል፡፡
ቻይና በሩሲያ እና በዩክሬን ግጭት ለደረሰው የዜጎች ጉዳት ትኩረት ትሰጣለች ያሉት ዋንግ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሰብአዊ ቀውሱን ለመቋቋም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡
ቻይና በዩክሬን ያለውን ሁኔታ በማቃለል ረገድ ገንቢ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች ሰብዓዊ ቀውሱን ለመከላከልም ቻይና የራሷን ጥረት ታደርጋለች ማለታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+7
0
People reached
151
Engagements
Boost post
144
2 Comments
5 Shares
Like
Comment
Share

