አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢንዱስትሪ ፓርኮች በስራ ዕድል ፈጠራና ውጭ ምንዛሬ የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያመጡ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ ፡፡
ከንቲባዋ የለቡ ሁዋጂያን ኢንዱስትሪ ፓርክን የጎበኙ ሲሆን÷ በተለይም ፓርኮቹ ምን አይነት ችግሮች እየገጠማቸው ነው፣ እንዴት ሊፈታ ይችላል፣ ከመንግሥት ምን ይጠበቃል የሚሉት በተለየ ትኩረት ታይተው ምላሽ የሚሰጣቸው ጉዳዮች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
የዚህ ጉብኝት ዋና ዓላማም ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት መሆኑንም ከንቲባ አዳነኝ አብራርተዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል::
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

