Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከመራጮች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ መራጮች ጋር እየተወያዩ ነው።

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተመርጠው ፓርላማ የገቡ የምክር ቤት አባላት የመረጣቸውን ህዝብ ማወያየት እንዳለባቸው በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የነዋሪውን ችግር ተረድተን ለመፍትሄውም እንተጋለንም ብለዋል ተመራጩ ዲያቆን ዳንኤል፡፡

የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በበኩላቸው÷ መሬት ላይ ያለውና በየመገናኛ ብዙሃኑ የሚወራው የተለያየ መሆኑን ጠቅሰው÷ በሁሉም ዘርፍ ከሌብነት ጋር ተያይዞ ሊታዩና ሊፈተሹ የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡

ከኑሮ ውድነት ጋር፣ ከሰላም፣ ከስራ እድል ፈጠራ፣ ከትምህርት፣ ከመልካም አስተዳደር እና ከሃይማኖት መቻቻል ጋር ተያይዞ ውይይት ተደርጓል፡፡

መንግስት ያለበትን ጫና እኛም እንጋራለን ያሉት ነዋሪዎቹ÷ ቀጣይም እንዲህ በቅርበት ውይይቶች ሊኖሩና ሊያዳምጠን ይገባል ብለዋል፡፡

በፈትያ አብደላ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version