አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልልና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ስልጠና በሀረር ከተማ ተጀምሯል።
በስልጠናው ላይ ከ580 በላይ የፓርቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ይሳተፉበታል።
በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ።
ስልጠናው በዋናነት የመደመር እሳቤ እና የብልፅግና ፓርቲ መሠረታዊ አስተሳሰቦች ምንነትና ይዘት ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተብሏል።
ከዚህ ባለፈም ሃገራዊ ለውጥና ከለውጡ ጋር ተያይዞ በተወሰዱ እርምጃዎች ላይ አመራሩ የተግባር አንድነት እንዲኖረው ለማድረግ ያግዛልም ነው የተባለው።
እንዲሁም የፓርቲው ፕሮግራሞችና አካሄድ ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲያዝ በማድረግ፥ አመራሩ በየደረጃው ከህዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችል አቅም እንዲገነባና ለቀጣይ ሀገራዊ ተልዕኮ እንዲዘጋጅ ለማድረግ በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑም ተጠቅሷል።
በተሾመ ሃይሉ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

