አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ከገረሴ ወረዳ ወደ አርባምንጭ ከተማ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ መኪና በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡
ተሕከርካሪው አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሼሌ መግቢያ ሲደርስ መገልበጡን የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ረታ ተክሉ ተናግረዋል።
ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በደረሰው አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ 13 ሰዎች ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉም ተብሏል፡፡
የአደጋው መንስዔ እየተጣራ መሆኑን የመምሪያው አዛዥ ገልጸዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision