Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ በአፈር መደርመስ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በአፈር መደርመስ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በወረዳው ቀበና ኪዳነ ምህረት አካባቢ ለህንፃ ግንባታ መሰረት በቁፋሮ ላይ እያሉ የተቆፈረው አፈር በሰዎች ላይ ተደርምሶ ነው የአንድ ሰው ህይወት ያለፈው፡፡
የኮሚሽኑ ፈልጎ ማዳን ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ አንድ ሰው ማትረፍ መቻሉንና ወደ ህክምና ማዕከል መወሰዱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
መጪው ጊዜ ክረምት በመሆኑ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ በግንባታ ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የግንባታ ባለሙያዎች እና የሚመለከተው አካል ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version