አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቻይና ኢስተርን አየር መንገድ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ በቻይና ኢስተርን አየር መንገድ በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።
በበረራ ቁጥር ኤም ዩ 735 በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ የተማሰቸውን ጥልቅ ሀዘን በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት እንዲሁም በራሳቸው ስም ለቻይና ህዝብና መንግስት ገልጸዋል።
በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

