አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ኤች አር 6600 ረቂቅ ህግን ያወጣቸው ለቀጠናው ሰላም በማሰብ ሳይሆን ፖለቲካዊ ፍላጎቷን ለማሳካት መሆኑን ጋዜጠኛ ፍራንሲስካ ሮንችን ተናገረች፡፡
ጣሊያናዊቷ ጋዜጠኛ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራት ቆይታ እንደተናገረችው ኤች አር 6600 ረቂቅ ህግ አሜሪካ ዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች ለኢትዮጵያና ኤርትራ የሚሰጡትን ብድር እንድትቃወም የሚደነግግ ሲሆን ህጉ የሚፀድቅ ከሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ ኑሮ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በእጅጉ የሚጎዳ መሆኑን ተናግራለች፡፡
አሜሪካ እነዚህ ረቂቅ ህጎች ለቀጠናው ሰላም፣ ዴሞክራሲ እና መረጋጋት አስተዋፅኦ አላቸው ብትልም አውነታው ግን ተቃራኒ ነው ትላለች ጋዜጠኛዋ፡፡
ማዕቀቡ በተለይም በኢትዮጵያ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በእጅጉ የሚጎዳ መሆኑን የገለፀቸው ጋዜጠኛዋ ይህም የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና የተባበሩት መንግስታት 2030 ዘላቂ የልማት አጅንዳዎች እንዳይፈፀሙ ምክንያት እንደሚሆንም አብራርታለች፡፡
እንደ ተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ሪፖርት በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ9 ሚሊየን በላይ ሰዎች መኖራቸው እየታወቀ አሜሪካ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሀገራትን ዘርፈ ብዙ ማዕቀብ እንዲጥሉ ግፊት ማድረጓ የሚያስተዛዝብ ነው ብላለች፡፡
አሜሪካ እና የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በአንድ በኩል የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲኖራቸው እና የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ እናግዛለን ይላሉ፤ በሌላ በኩል ግን የአፍሪካን ሕዝብ በሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ ጥገኛ ለማድረግ ማዕቀቦችን እያስፋፉ ነው ስትል ትገልጻለች፡፡
አሜሪካ እውነተኛ አላማዋ የአፍሪካ ሀገራትን በእርዳታ ላይ ጥገኛ ማድረግ እና የእጅ አዙር ቅኝ ተገዢ ለማድረግ ካልሆነ በአፍሪካ ሀገራት ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦችን ማቆም አለባትም ብላለች ጋዜጠኛዋ፡፡
በሚኪያስ አየለ እና በወንድወሰን አረጋሕኝ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

