አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግንባታቸው እየተከናወኑ ያሉ ልዩ ልዩ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ጎበኙ ፡፡
በርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልዑክ የአርባምንጭ 2ኛ ደረጃ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት ግንባታ እንዲሁም 8 ነጥብ 7 ኪ/ሜ የሚሸፍነውን የከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ስራ ግንባታንም ጎብኝተዋል።
የከተማውን ህብረተሰብ የጤና ተደራሽነት ለማሳደግ እየተገነባ ያለውን የአዲስ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ሂደት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የኩልፎን ወንዝ ዳርቻን ተከትሎ እየለማ ያለ አረንጓዴ ፓርክ እና አዳሪ ትምህርት ት/ቤት እንደተጎበኘም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

