አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ አባልና የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳዳት ነሻን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በ 150 ሚሊየን ዶላር ወጪ ተገንብቶ ከሁለት ዓመት በፊት በጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ አሕመድ ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል፡፡
በተጨማሪም ከድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጀዋር እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ህግና ስርዕት ከማስፈን እያከናወነ የሚገኘውን የለውጥ ስራ ጎብኝተዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

