አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በብልጽግና ፓርቲ ቀጣይ አቅጣጫዎች እና በ1ኛ ጉባኤው ውሳኔዎች ዙሪያ በሰመራ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት መካሄድ ጀምሯል።
በውይይቱ የክልሉ ርዕሠ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ አወል አርባ፣ የገንዘብ ሚኒስትር እና የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ አቶ አህመድ ሽዴ እና የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙ እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ በፓርቲው 1ኛ መደበኛ ጉባኤ በተቀመጡ አቅጣጫዎች፣ ውሳኔዎችና አቋሞች ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ይፈጠራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአፋር መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

