Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ሕፃናትን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ሊተገበር ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜንና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በአራት ወረዳዎች በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ሕፃናትን የትምሕርት ተጠቃሚ የሚያደርግ የ81ሚሊየን ብር ፕሮጀክት ሊተገበር ነው።
በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የአማራ ክልል ዳይሬክተር አቶ አሰፋ እሸቴ÷ በምዕራብና ምሥራቅ አማራ በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም 300 ሚሊየን ብር ተመድቦ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በትምሕርት፣ በጤና፣ በግብርና እና በውኃ ዘርፍ በርካታ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን የገለጹት አቶ አሰፋ÷ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ቁጥር 1 እና 2 ወረዳዎች እንዲሁም በሰሜን ጎንደር ዞን በዳባትና ደባርቅ ወረዳዎች በጦርነቱ ምክንያት ከትምሕርት ገበታ ውጭ የሆኑ ሕፃናትን ለማስተማርና ከጾታዊ ጥቃት ለመከላከል ያለመ ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል ሴቶች ሕፃናት ማሕበራዊ ጉዳይ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሰላማዊት ዓለማየሁ በበኩላቸው÷ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በማሕበራዊ ዘርፍ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
አዲስ የሚተገበረው ፕሮጄክትም በተሟላ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ፕሮጄክቱ 25 ሺህ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተመላክቷል፡፡
በምናለ አየነው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version