አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጦርነቱ የተጎዱ ከ227 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ135 ሚሊየን ብር ኘሮጀክት ይፋ አደረገች ፡፡
ቤተክርስቲያኗ በትግራይ፣ አማራ፣ አፋርና ኦሮሚያ ክልሎች በጸጥታ ችግር እና ጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም የሚውል ኘሮጀክት ነው ዛሬ ይፋ ያደረገችው።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ፀሀፊ ዶክተር አባ ተሾመ ፍቅሬ ኘሮጀክቱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ፥ ቤተክርስቲያኗ በርካታ የልማት እና እርዳታ ስራዎች ስትሰራ መቆየቷን ተናግረዋል።
ዛሬ ይፋ የተደረገው ኘሮጀክት ለችግር የተጋለጡ ወገኖች እና ተፈናቃዮችን ተቀብለው የሚያስተናግዱ ማህበረሰቦችን የኑሮ ሁኔታ በመሰረታዊ የእርዳታ አቅርቦት እንዲታገዝ ያደርጋል ብለዋል።
በቅድስት አባተ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

