አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጥራት በታች የሆኑ 130 የሚሆኑ ማሸነሪዎች ከስራ እንዲወጡ እና አምስት የህንጻ ግንባታ ስራዎች በጥራት ጉድለት ምክንያት እንዲፈርሱ መደረጉን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ገለጸ፡፡
ባለስልጣኑ ከአጋር አካላት ጋር በደሴ ከተማ ዘርፉን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ ሲሆን፥ በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ሁሉም አካላት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ነገዎ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ እንደዛሬው ቴክኖሎጂ ባልተስፋፋበት ዘመን ግንባታን ከመሬት ሳይሆን ከላይ ወደ ታች በመከወን እንደ ላሊበላ ያሉ ድንቅ የግንባታ ሂደትን ለዓለም ያሳየች ሀገር ናት መሆኗን ጠቅሰዋል።
በኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሰሩ ባለቤቶች፣ አማካሪዎችና ስራ ተቋራጮች በጋራ በመሆን በዘርፉ የሚታየውን የጥራትም ይሁን የግንባታ ጊዜ መጓተት ሊያስቀሩ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በቀደምት ጊዜያት በኪነ ህንጻም ይሁን በግንባታ ልህቀት ያላትን የጥንት ገናናነት በጋራ ማስመለስ ይገባል ነው የተባለው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት ሶስት ዓመታት 381 ኘሮጀክቶችን ዲዛይን ያደረገ ሲሆን÷ 151 የሚሆኑ ኘሮጀክቶች ላይ ቁጥጥር ማድረጉ ተገልጿል።
ከ129 በላይ ማሸነሪዎች ከጥራት በታች በመሆናቸው ከስራ እንዲወጡ አድርጌለሁ ያለው ተቋሙ ፥ አምስት የህንጻ ግንባታ ሰራዎች በጥራት ጉድለት ምክንያት እንዲፈርሱ ተደርጓል ብሏል።
በውይይቱ የአዲስ አበበ አባባ፣ የአፋርና አማራ ክልሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ችግሮችን መቅረፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እያደረጉ ነው።
በከድር መሀመድና አለባቸው አባተ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

