አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በህወሓት አሸባሪ ቡድን ለተፈናቀሉ የአማራና አፋር ክልሎች ዜጎች 18 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የገንዘብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ ማሰባሰቡን አስታወቀ፡፡
ድጋፉም ምግብ፣ የቤት መስሪያ ቁሳቁስ፣ የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣ የቤትና የህክምና ቁሳቁስን ያካተተ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙና የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሀላፊ አቶ መለሰ አባተን ጨምሮ የተለያዩ የሊጉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
አቶ መለሰ ዓለሙ ፥ “ወጣቶች በየዘመኑ የሚሰጣቸው ተልዕኮ አለ፤ የዚህ ዘመን ወጣቶች ተልዕኮ ደግሞ ሀገርን ማዳን ነው” ብለዋል፡፡
“በዚህ ወቅትም ለሀገራችን አለን በማለታችሁ ከፍተኛ ኩራት ይሰማናል” ነው ያሉት፡፡
የገጠሙንን ፈተናዎች በጋራ በመረባረብ እናልፋቸዋለን ያሉት አቶ መለስ ዓለሙ ፥ “ምንም እንኳን ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙንም ከትናንትናው አይብሱም እንሻገራቸዋለን” ነው ያሉት፡፡
“ከወጣቱ ብዙ ይጠበቃል የተጀመረው ተግባር አርዓያ የሚሆን ነው፤ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም” ብለዋል፡፡
የተሰበሰበው ሀብት ከዛሬ ጀምሮ ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች እንደሚሰራጭ ተነግሯል፡፡
በዘቢብ ተክላይ
ምስል ፡- ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

