Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪ ግለሰብ ከ25 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪ ግለሰብና ግብረ አበሩ ከ25 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

መነሻቸውን ከአማራ ክልል ባሕርዳር ከተማ ያደረጉት ህገ ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪውና ግብረ አበሩ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3 A03861 በሆነ አፍሪካ ባስ በተባለ የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት በቁጥር 25 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች በመጫን እያሽከረከሩ መዳረሻቸውን አዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ በመጓዝ ላይ እያሉ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ግለሰቦቹ በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተብሎ በሚጠራው ልዩ ቦታ ሲደርሱ ከነጦር መሣሪያቸው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version