አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ 39 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
34 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ሲሰራ የቆየው ቢሮው÷ 39 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን ለታማኝ ግብር ከፋዮችም እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።
በእንጦጦ ፓርክ በተካሄደው መርሀ ግብር በ2013 በጀት ዓመት በአግባቡ እና በወቅቱ የሚጠበቅባቸውን ግብር ለከፈሉ ለታማኝ ግብር ከፋዮች ነው እውቅና እና ሽልማት የተሰጠው።
በመርሀ ግብሩ ግብር ከፋዮቹ በደረጃ የብር፣ የወርቅና የፕላቲኒየም ተሸላሚዎች ሆነዋል።
በ2013 ዓ.ም የግብር ግዴታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር የተከናወነው ̎የላቀ ገቢ ለከተማችን ብልፅግና“በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ እንደገለጹት÷ ለከተማዋ ልማትና ብልፅግና ለሚደረገው ርብርብ የላቀ አስተዋፅኦ ለነበራቸው እውቅና መስጠት ለሌሎች መነሳሳትን ይፈጥራል።
ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ በሀገሪቱ ለተከሰተው ለኮሮና ቫይረስ፣ ለሕግ ማስከበር ዘመቻ፣ ለህዳሴ ግድብ እና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ታማኝ ግብር ከፋዮችን አመስግነው÷ ለብር፣ ለወርቅ እና ለፕላቲኒየም ተሸላሚ ግብር ከፋዮች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ከምትጠብቀው ግብር በተጨማሪ በተለያየ ዘርፍ ግብር ከፋዮች ያደረጉት አስተዋጽኦ ቀላል አለመሆኑን አንስተዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

