አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመን ዘርፍ ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችል የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የቢዝነስ ፎረሙ ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 125ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የሚካሄድ መሆኑን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ፎረሙ በሀገራቱ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ተናግረዋል፡፡

