አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ቀዳሚ ትኩረት በሰጠባቸው የግብርና ልማት ዘርፎች ላይ የልማት አጋሮች ትብብር አስፈላጊ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለፁ።
ሚኒስትሯ ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ማዊራ ቺቲማ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይ ዶክተር ፍጹም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ሰፊ የግብርና ዘርፍ የማጠናከርና የማዘመን ሥራ በተመለከተ አንስተዋል።
መንግሥት በግብርና ልማት ዘርፍ በተለይም ለመስኖ እና የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ቀዳሚ ትኩረት እንደሚሰጥ የጠቀሱ ሲሆን፥ በእነዚህ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የልማት አጋሮች ትብብር አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የሚገኘው የዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ በዓለማችን 98 ሀገራት 237 ፕሮጀክቶችን ያንቀሳቅሳል።
የልማት ፈንዱ በአሁኑ ሰዓትም በአገራችን ኢትዮጵያ ሦስት ግዙፍ ፕሮጅክቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
እነዚህን ሦስት ፕሮጀክቶች በተመለከተ ሒደቱ ላይ ማብራሪያ የሰጡት ማዊራ ቺቲማ፥ የዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ በቀጣይ ይፋ ሊያደርገው ስለተሰናዳው አሳታፊ የግብርና እና የአየር ንብረት ለውጥ የተሰኘ ፕሮግራም ላይም ገለጻ ሰጥተዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹንም የዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ፣ የግሪን ክላይሜት ፈንድ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክን የመሳሰሉ ተቋማት በገንዘብ እንደሚደግፉትም ተገልጿል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

