Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ቀጠናዊ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉበት አግባብ ላይ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ቀጠናዊ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉበት አግባብ ላይ ምክክር ተካሄደ።

ምክክሩ በጂቡቲ ወደቦችና ነጻ ቀጠና ባለስልጣን ሊቀ መንበር አቡበክር ኦማር ሃዲ እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ምህረቱ ማሞ መካከል ነው የተካሄደው።

በውይይታቸው ወቅትም በጋራ የሚያከናውኗቸውን የልማት እንቅስቃሴዎች ማሳደግ በሚቻልባቸው እንዲሁም በሌሎች የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ምህረቱ ማሞ በዚህ ወቅት ሃገራቱ በጋራ የሚያከናውኗቸው የመሰረተ ልማት ፕሮጄክቶች የሃገራቱን ቀጠናዊ ትስስር ለማጠናከር እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version