Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

“ኢትዮጵያን ለማዳን አካታች ብሔራዊ ምክክር” በሚል መሪ ሃሳብ የፖናል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያን ለማዳን አካታች ብሔራዊ ምክክር” በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይት ተካሂዷል፡፡
የፖናል ውይይቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ኢኒስቲትዩት እና አይ ኤስ ኤስ በጋራ ያዘጋጁት መሆኑ ተገልጿል፡፡
መደረኩ በኢትዮጵያ የተሳካ አገራዊ ምክክር የማካሄድ አስፈላጊነትና ቅድመ ሁኔታዎች፣ ብሔራዊ ምክክር ከማካሄድ አኳያ ያሉ ዓለምአቀፍ ተሞክሮዎችና ታሪካዊ አንድምታ፣ አገራዊ ምክክርን ለማካሄድ የኢትዮጵያ አቅም እና በሌሎች ሃሳቦች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ የተገኙት በሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን ÷ለረጅም ጊዜያት የቆዩ አገራዊ ችግሮችን በብሔራዊ ምክክር ለመፍታት በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ መንግስት ሂደቱን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡
የፖናል ውይይት ተሳታፊዎችም ለአገራዊ ምክክር ሂደቱ ይበጃል ያሏቸውን ሃሳቦች አንስተው መወያየታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version