አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ 10 የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞስኮን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟ ተሰምቷል፡፡
ዲፕሎማቶቹ የሞስኮን ገጽታ ለማበላሸት ተንቀሳቅሰዋል በሚል ነው ከሩሲያ እንዲወጡ የታዘዙት፡፡
ከሩሲያ እንዲወጡ የታዘዙትም የኢስቶኒያ፣ላቲቪያ እና ሊውትኒያ ዲፕሎማቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የሊውትኒያ አራት የኤምባሲ ሰራተኞች፣ ሶስት የላትቪያ ኤምባሲ ድፕሎማቶችን እንዲሁም ሶስት የኢስቶኒያ ተወካዮችን በድምሩ 10 ዲፕሎማቶችን ከሞስኮ እና ከሴንት ፒተርስበርግ እንዲወጡ መታዘዛቸውን የሩሲያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባደረሰችው ወታደራዊ ጥቃት በምዕራቡ ዓለም እና በሞስኮ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ጦርነት በከፍተኛ ሁኔታ የተባባሰ ሲሆን÷ በርካታ የአውሮፓ አገራት ቀደም ሲል የሩሲያ ዲፐሎማቶችን አባረዋል፡፡
በዚህ ወር ፖላንድ በስለላ የጠረጠረቻቸውን 45 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ከአገሯ ያስወጣች ሲሆን ÷ በተመሳሳይ ቤልጂዬም፣ አየርላንድ እና ኔዘርላንድስ በድምሩ ከ40 በላይ የሩሲያ ዲፕሎማቶችን ከሀገራቸው አባረዋል፡፡
ከውሳኔው በኋላ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ÷ የሩሲያ ዲፕሎማቶች መሠረተ ቢስ መባረር ተገቢ ምላሽ ያገኛል ብሏል፡፡
የላትቪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤድጋርስ ሪንኬቪክስ በበኩላቸው÷ የሩሲያ ባለስልጣናት የሀገራቸውን ዲፕሎማቶች ያለምክንያት እንዳባረሩ ማባረራቸውን ገልፀዋል፡፡
ከዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ጋር ተያይዞ ምዕራባውያን ሀገራት ዲፕሎማሲያቸው እየተቀዛቀዘ መሆኑን አር ቲ በዘገባው አመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

