አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፍትህ ሚኒስቴር እና በክልል ፍትህ ቢሮዎች መካከል በህግ እና ፍትህ ማሻሻያ ዙሪያ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ የፍትህ ሚኒስትር ዶክተር ጌዴዮን ጢሞቴዎስ፣ የመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አወል ሱልጣን፣ የሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የፍትህ ዘርፉ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ተመራማሪዎች እየተካፈሉ ይገኛሉ።
ለሶስት ቀናት ተካሂዶ ዛሬ በሚጠናቀቀው የምክክር መድረክ የተሞክሮ ልውውጥ እየተካሄደ ይገኛል።
የህግ አካላት ኃላፊነት፣ የህግ ማርቀቅ እና የማረም ስራዎች ሂደት፣ ህጎችን የማጠቃለል የህግ ዘርፉን ለማዘመን የተሰሩ ስራዎች እና መሰል ተግባራት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።
የፌደራል ህጎችን ተፈጻሚነት የተመለከቱ እና መሰል የፍትህ ዘርፉን የተመለከቱ ጉዳዮች በአቶ አለምአንተ አግደው የመንግስት ህግ እና ፍትህ አገልግሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ቀርበው የተሞክሮ ልውውጥ ተካሂዶባቸዋል።
በለይኩን ዓለም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

