አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በጉባኤው የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁን ጨምሮ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና የአባል አገራቱ የትምህርት ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል።
ጉባኤው አካታች፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለስደተኞች፣ ከስደት ተመላሾች እንዲሁም ስደተኞችን ተቀብለው እያስተናገዱ ያሉ ማህበረሰቦች የሚያገኙበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም በጉባኤው በፈረንጆቹ ታህሳስ 2021 በጅቡቲ ተካሂዶ በነበረው ጉባኤ በቀጣናው በትምህርት ዙሪያ ለመስራት የተያዙ እቅዶችን በሚመለከት ውይይት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በጉባኤው ኢትዮጵያን ጨምሮ የጅቡቲ፣ ኬኒያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እና የሱዳን ትምህርት ሚኒስትሮች እና የሚኒስትሮች ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

