Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የስልጤ ህዝብ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ከጀመረ በኋላ ዘርፈ ብዙ ለውጦችን አስመዝግቧል – ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስልጤ ህዝብ ራሱን በራሱ ማስተዳደር ከጀመረ በኋላ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ለውጥ ማስመዝገቡን የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎ ተናገሩ፡፡

አፈ ጉባኤዋ በ15ኛው የስልጤ ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚዬም መድረክ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የስልጤ ህዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ባደረገው ትግል መጋቢት 23 ቀን 1993 ዓ.ም የዞን አደረጃጀት ጥያቄው መመለሱን አስታውሰዋል፡፡

ህዝቡ በዞን ከተደራጀ በኋላም በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዘርፎች መጠፈ ሰፊ እምርታዎችን አስመዝግቧል ነው ያሉት፡፡

ማህበረሰቡን በማስተባበር በትምህርት ተሳትፎ፣ በግብርና፣ በመንገድና መሰረተ ልማት፣ በኢንቨስትመንት እንዲሁም በሴቶች እና ወጣቶች ተጠቃሚነት ዙሪያ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መከናወናቸውንም አፈ ጉባኤዋ አውስተዋል፡፡

የዞኑ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም መጋቢት 23 ቀን የሚከበርበት ዋናው ምክንያት የህዘቡን ቋንቋ እና ባህል ለማሳደግ በማሰብ መሆኑን የገለፁትወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ ፥ እስካሁን በተደረገው ጥረትም ስልጤኛ ቋንቋ ከመግባቢያነት አልፎ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እስከ መሰጠት መድረሱን አብራርተዋል፡፡

በዚህ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚዬም በተለያየ አካባቢ የሚኖሩ የዞኑ ነዋሪዎች የተሳታፉ ሲሆን ፥ ለዞኑ እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version