Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በባሕርዳር ከተማ በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ዘመናዊ ድልድይ 60 በመቶ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕርዳር ከተማ በዓባይ ወንዝ ላይ በ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው ዘመናዊ ድልድይ ግንባታ 60 በመቶ መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

የከተማዋ ኮንስትራክሽን ልማት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ገበያው በላይ ÷ ለረጅም ዓመታት እያገለገለ የሚገኘው ድልድይ አሁን ያለውን የትራፊክ ፍሰት የማስተናገድ አቅሙ ዝቅተኛ በመሆኑ አዲስ ድልድይ መገንባት ማስፈለጉን ተናግረዋል።

የድልድዩን ግንባታ በፈረንጆች 2022 መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን ግንባታውን የሚያከናውነው የቻይና ኩባንያ የሥራ ኃላፊ ዜን ይ ተናግረዋል።

የድልድዩ መገንባት ከሚሰጠው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባለፈ ለከተማዋ ገጽታ ጥሩ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ እና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶችንም ውጤታማ ለማድረግ እንደሚያግዝ ተመላክቷል።

በለይኩን ዓለም

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version