Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሻሸመኔ ከተማ 200 ኪሎ ግራም የሚመዝን የካናቢስ አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻሸመኔ ከተማ ትናንት ማታ በተደረገ አሰሳ 200 ኪሎግራም የሚመዝን ካናቢስ አደንዛዥ ዕፅ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የመምሪያው ህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ታምራት አበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከሰሞኑ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በከተማዋ የሚስተዋሉ ህገ ወጥ ተግባራት ላይ ክትትል እየተደረገ ነው፡፡

በከተማዋ በተደረገ የተቀናጀ ክትትልም 200 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ መያዙን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ዕፁን ለመመዝን የሚያገለግሉ ሶስት ሚዛኖችን ጨምሮ ወንጀሉን በመፈጸም የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ባሳለፍነው ሳምንት 400 ኪሎ ግራም የሚመዝን የካናቢስ አደንዛዥ ፅጽ በቁጥጥር ስር አውሎ እንደነበርም ኢንስፔክተሩ አስታውሰዋል፡፡

ትናንት ምሽት የተያዘው ካናቢስ አደንዛዥ ዕፅም ታሽጎ በሞያሌ በኩል ለውጭ ገበያ ሊወጣ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

በሻሸመኔ ከተማና አካባቢዋ የካናቢስ አደንዛዥ ዕፅ በሰፊው እንደሚመረትና እንደሚንቀሳቀስ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በተለያዩ ዘገባዎች ማመላከቱ ይታወሳል፡፡

በጌታቸው ሙለታ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version