Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ በዘንድሮው የበጋ ልማት በዘር ከተሸፈነ የስንዴ ማሳ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚሰበሰብ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ ልማት 40 ሺህ ሄ/ር መሬት ላይ ከተሸፈነው የስንዴ ማሳ ከ1 ሚሊየን 500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚሰበሰብ ተገለፀ፡፡
በክልሉ በ 2014 ዓ.ም በመስኖ በበጋ የለማው ስንዴ አሰባሰብና ወደ ገበያ አቀራረብ በተመለከተ የክልሉ ግብርና ቢሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሂዷል፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ የግብአት አቅርቦት ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ወይዘሮ ሙሽራ ÷ በ2013 ዓ.ም 13 ሺህ ሄ/ር መሬት በመስኖ ስንዴ የለማ መሆኑን እና በ 2014 ዓ.ም ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ወደ 40 ሺህ ሄ/ር ማሳደግ መቻሉን አብራርተው ባለፈው አመት ከልማቱ ባሻገር ወደ ገበያ ማቅረብ ላይ አለመሰራቱን አስታውሰዋል፡፡
ከዚህ በመነሳትም በዚህ ዓመት የሚመረተውን ስንዴ በጥራት ተሰብስቦ፤ግዢ አካሂዶ ለገበያ ማቅረብ አስፈላጊ በመሆኑ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር ማድረግ አስፈልጓል ብለዋል፡፡
የግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ በአቶ አጀበ ስንሻው÷ በአማራ ክልል በዘንድሮው የበጋ ልማት 40 ሺ ሄ/ር ከሸፈነው የስንዴ ማሳ ከ1ሚሊየን 500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚሰበሰብ እና ከዚያ ውስጥ ሰላሳ መቶኛው 468 ሺህ ኩንታል ግዢ ለመፈጸም ዕቅድ መያዙን ገልጸዋል፡፡
አቶ አጀበ ስንሻው የበጋ ስንዴ ለማልማት የተሰጠውን ልዩ ትኩረትና ርብርብ ለሰብሉ አሰባሰብ፤ግዢና ገበያ አቅርቦት ላይም ትኩረትና ርብርብ እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version