አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ልምድ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሚያስተዋውቅ ኮንፈረንስ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው በመጪው ሐምሌ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ኮንፈረንስ የቅድመ ዝግጅት ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዷል።
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ እንድሪስ እንዳሉት፤ ኮንፍረንሱ በተለያዩ የአለም አገሮች የሚገኙና በአካባቢ ጥበቃ፣ በደን ልማት፣ በግብርና እና በውኃ ሣይንስ ምህንድስና ሙያ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን እንዲዘጋጅ የቀረበ ሃሳብ ነው።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ምጣኔ ሃብት በመገንባት በምግብ እራሷን ለመቻል እያከናወነች ላለው ተግባር የአረንጓዴ አሻራ አስተዋጽኦው የጎላ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በአረንጓዴ አሻራ የተገኘውን ልምድ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚያስተዋውቀው ኮንፈረንስ ውጤታማ እንዲሆን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እንደሚሰራ አስታወቀዋል።
በኢትዮጵያ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የአረንጓዴ አሻራውን እንደሚያሳርፈው ሁሉ፤ ዳያስፖራውም በተለያየ መንገድ አሻራውን እያሳረፈ መሆኑን ዶክተር መሀመድ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በሚዘጋጀው የአረንጓዴ አሻራ የገጽታ ግንባታ ኮንፈረንስ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአረንጓዴ አብዮት ዕውቅናና የኖቤል ሽልማት ያገኙ ግለሰቦች እንደሚያሳተፉም ነው የተናገሩት።
በኮንፈረንሱ 40 የሚጠጉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁና በአካባቢ ጥበቃና በአየር ንብረት ሽልማት ያገኙ ተቋማትና ግለሰቦች እንደሚጋበዙም ጨምረው ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ ከአገር ውስጥና ከውጭ ካሉ ድርጅቶችና ሙያተኞች ጋር በአጋርነት የፖሊሲ ሀሳብና የድርጊት መርሃ ግብር በመንደፍ አውደ ጥናትና ኮንፈረንስ ይዘጋጃል ተብሏል።
በአገር ውስጥና በውጭ ያሉትን ሙያተኞችን ለማገናኘት ምክር ቤታቸው ዋና ዓላማ አድርጎ መነሳቱንም የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

