Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ እርስቱ ይርዳ በጉራጌ ዞን እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በጉራጌ ዞን ከ383 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ብር በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለውን የከሪብ መስኖ ፕሮጀክት እየጎበኙ ነው።
 
በዞኑ 1660 ሄክታር መሬት ያለማል ተብሎ የሚጠበቀው የከሬብ መስኖ ፕሮጀክት የግንባታው ሂደት 62 በመቶ ደርሷል።
 
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ፕሮጀክቱን በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት÷ፕሮጀክቱ በበጀት እጥረት፣በአካባቢዉ የመሬት አቀማመጥ፣በፋብሪካ ጥሬ እቃ አቅርቦት እና በመሠል ችግሮች የግንባታው ሂደት በሚፈለገው ልክ መጓዝ አልቻለም።
 
የክልሉ መንግስት ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ህብረተሰቡ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚተገበሩ የልማት ፕሮጀክቶች መሳካት ትብብር እንዲያደርግም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version