Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተተኳሽ ጥይቶችን ደብቆ ለማሳለፍ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ተተኳሽ ጥይቶችን በህገ ወጥ መንገድ በጭነት ተሽከርካሪ ላይ ደብቆ ለማሳለፍ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር የዋለው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 -6189 አ.አ. በሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ 404 ተተኳሽ ጥይቶችን በዱቄት ከረጢት ውስጥ ደብቆ በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ዲሬ ጉዶ ከተማ ማዞሪያው አካባቢ እንደደረሰ መሆኑን የወረዳው ፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር ቶሎሳ መልካ ገልጸዋል።

ተተኳሽ ጥይቶቹ ለፀረ ሰላም ሃይሎች ለማስተላለፍ እንደሆነ መጠርጠሩን ያመለከቱት ኮማንደር ቶሎሳ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ያሉት ኮማንደር ቶሎሳ፥ ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመተባበር ወንጀልን እንዲከላከል ጠይቀዋል፡፡

በወረዳው በተያዘው ወር ብቻ የአሁኑን ሳይጨምር 862 ተተኳሽ ጥይቶች መያዛቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version