አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ምርመራና ጥናት ማዕከል ለኮምቦልቻና ሲዳማ የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የላብራቶሪ መሳሪያ ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉንም የኮምቦልቻ እና ሲዳማ የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ ተወካዮች ሰበታ በሚገኘው የማዕከሉ ግቢ በመገኘት ተረክበዋል።
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋዬ ሩፋኤል በርክክቡ ወቅት ÷ ማዕከሉ ለኮምቦልቻ ላብራቶሪ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እና ለሲዳማ ላብራቶሪ ደግሞ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።
ድጋፉም የኮምቦልቻ የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን በመውደሙ ዳግም በተጠናከረ ሁኔታ ስራ እንዲጀምርና እንዲደራጅ ያስችላቸዋል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
የሲዳማ ክልል የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ ደግሞ በመቋቋም ላይ በመሆኑን አዲስ ላብራቶሪ ስራ ማስጀመሪያና ማቋቋሚያ የሚውል ነው ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የኮምቦልቻ እና የሲዳማ የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ ተወካዮችም ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው በተደረገላቸው ድጋፍም የተሻለ ስራ በመስራት ለእንስሳት ጤና መጠበቅ የሚተጉ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

