Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሲዳማ ክልል በህዝብ የተነሱ ጥያቄዎች በሚፈቱበት መንገድ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ውሳኔን ተከትሎ በሲዳማ ክልል በሁሉም አካባቢዎች በተካሄዱ ህዝባዊ መድረኮች ላይ የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎች በሚፈቱበት መንገድ ላይ ውይይት ተካሄደ።
በሲዳማ ክልል በሁሉም አካባቢዎች በተካሄዱ ህዝባዊ መድረኮች ላይ የተነሱ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ የሶስት ወራት ዕቅድ በማዘጋጀት ጥያቆዎች በሚፈቱበት መንገድ ላይ ከክልሉ፣ ከወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች አመራሮች ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን ፥ በመድረኩም ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች አመራሮች ተገኝተዋል።
አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንደተናገሩት፥ የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ውሳኔዎችን መነሻ በማድረግ ከህዝቡ ጋር በተደረገው ውይይት የተነሱ ጥያቄዎች የሚመለሱበት የሦስት ወራት ዕቅድ በማዘጋጀት በፍጥነት የህዝብን ጥያቄ መመለስ በምንችልበት መንገድ ላይ ከአመራሩ ጋር መግባባት በመፍጠር ወደ ስራ የምንገባበት ልዩ መድረክ ነው ብለዋል።
አያይዘውም ህዝብ በፓርቲው ላይ ተስፋ በማሳደር ያነሳቸው የመልካም አስተዳደር፣ የስራ አጥነት ችግሮች፣ ብልሹ አሰራሮች፣ ህዝቡን ያስመረሩ የኑሮ ውድነት ጉዳዮች እንዲሁም የልማት፣ የሰላምና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በርካታ ጥያቄዎችን ማንሳቱን በመጥቀስ፥ ጥያቄውን ባጠረ ጊዜ ለመፍታት ሁሉም አመራር ቁርጠኝነትን በመላበስ መንቀሳቀስ እንዳለበት አሳስበዋል።
የህዝብ ጥያቄን ለመመለስ በበጀት ዓመቱ ቀሪ ሶስት ወራት ዕቅዶችን በማዘጋጀት ከመደበኛ ስራዎች ጎን ለጎን በተለየ ትኩረትና ተጠያቂነት የሚፈታበት መንገድ ላይ ከክልሉ ህዝብ ጋር በመቀራረብ እንደሚሰራ የፓርቲው ፅህፈት ቤት ኃላፊ መግለጻቸውን ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version