Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተመድ በቡቻ የተፈጸመውን ግድያ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጥሪ አቀረበ

አዲሰ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩክሬኗ ከተማ ቡቻ የተፈፀመውን የንፁሀን ዜጎች ግድያ ገለልተኛ አካል እንዲያጣራው የመንግስታቱ ድርጅትዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጉቴሬዝ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት የሞቱ የንፁሀን ዜጎችን ምስል በማየቴ ተረብሻለሁ፤ ገለልተኛ አካላት የተፈፀመውን ድርጊት በማጣራት ወንጀለኞችን ተጠያቂ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡
 
ከቀናት በፊት በኬቭ አቅራቢያ በምትገኘው ቡቻ ከተማ እስካሁን 410 የሚሆኑ ንፁሀን ዜጎች በከተማዋ መገደላቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።
ዩክሬን ንፁሀን በሩሲያ ተገድለዋል ስትል ውንጀላ አቅርባለች።
 
በአንጻሩ ሩሲያ ጉዳዩ የዩክሬን ድራማ እንጅ የሩሲያ ወታደሮች ድርጊት አይደለም ስትል አስተባብላለች፡፡
 
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በጉዳዩ ዙሪያ የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
 
የተለያዩ ሀገራት መሪዎችም በግምት ሩሲያን ከመወንጀል እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡
 
በኬቭ የቀረበው ክስ መሰረተ ቢስ ነው ያሉት ፔስኮቭ ግድያውን በተመለከተ የወጡ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ሀሰተኛ መሆናቸውን የሩሲያ ወታደራዊ ባለሙያዎች ማረጋገጣቸውን ገልፀዋል፡፡
ስለሆነም ሞስኮ የቡቻን የንፁሀን ዜጎች ግድያ በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለመወያየት እንደምትፈልግ ቃል አቀባዩ መግለፃቸውን አር ቲ እና ሲ ጅ ቲ ኤን ዘግበዋል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version