Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮሚሽኑ በአማራ ክልል ከ3 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተመድቦ የሴፍቲኔት ፕሮግራሞ ተግባራዊ እየተደረገ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በዘንድሮ በጀት ዓመት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቦ ልማታዊ የሴፍቲኔት ፕሮግራሞ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ምግብ ዋስትና አደጋ መከላከል ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በክልሉ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም አፈጻጸም የአጋር አካላትን ተሳትፎ ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ በጎንደር ከተማ ዛሬ ተካሄዷል፡፡
 
የኮሚሽኑ የምግብ ዋስትና ዳይሬክተር አቶ ወርቁ ከበደ ÷ በክልሉ 11 ዞኖች በሚገኙ 87 ወረዳዎች ፕሮግራሙ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው÷በክልሉ በምግብ ዋስትና እጦት በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ይደረጋል ብለዋል፡፡
 
በክልሉ በፕሮግራሙ ታቅፈው የነበሩ ከአንድ ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ባለፉት ዓመታት የምግብ ዋስትናቸውን በማረጋገጣቸው ከፕሮግራሙ መሰናበታቸውን ገልጸዋል፡፡
 
የመስራት አቅም ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከ650 ሚሊየን ብር በላይ የተዘዋዋሪ ብድር መመቻቸቱን ጠቁመው÷ብድሩ ሀብትና ጥሪት እንዲያፈሩ የሚያግዛቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
 
የክልሉ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች በፕሮግራሙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን የገለፁት ደግሞ በክልሉ ግብርና ቢሮ የማህብረሰብ ልማት ስራዎች አስተባባሪ አቶ ደለለኝ አዱኛ ናቸው፡፡
 
የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሃይለማርያም ከፍያለው በበኩላቸው በክልሉ በልማታዊ ሴፍቲኔት የሚከናወኑ የልማት ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን አመልክተዋል።
 
ለውጤታማነቱም የአጋር አካላት ትብብርና ተሳትፎ የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
ፕሮግራሙ በገጠር አካባቢዎች የሚስተዋለውን ስር የሰደደ ድህነት ለመቀነስ የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመው በበጀት አመቱ ሊከናወኑ የታቀዱ ተግባራት በወቅቱ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ መትጋት እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version